የህንድ ሆስፒታሎች በኮቪድ-19 ታማሚዎች በመሙላታቸው ህሙማን ተቸግረዋል

ሚያዝያ 19/2013 (ዋልታ) – በሕንድ ደልሂ እና ሌሎች ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ሆስፒታሎች ብዙዎቹ ያላቸው አልጋ በህሙማን መያዛቸው ብቻ ሳይሆን የኮቪድ-19 ህክምና መስጫዎች መሳሪያ ዋጋ እጅግ በመጨመሩ የከፋ ችግር አጋጥሟል።

ለመተንፈስ የሚያግዙ መሳሪያዎች፣ የኦክሲጅን ሲሊንደሮችና ሌሎች ተዛማጅ የህክምና ቁሳቁሶች ዋጋ ጣራ መንካቱም ተገልጿል።

በሆስፒታሎች ህክምና ማግኘት ያልቻሉ ሰዎች በቤት ውስጥ ህመምተኞች ህክምና የሚያገኙበትን መንገድ እንዲያገኙ ማስገደዱ ላይ የአስፈላጊ የህክምና መሳሪያዎች መጥፋት ችግሩን እንዳከፋውም ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።