የህወሃት ጥቃት የሚያወግዝና ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው

የህወሃት ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የአሸባሪውን ህወሃት ጥቃት የሚያወግዝ እና ለሀገር አንድነት ውድ ሕይወቱን እየከፈለ ላለው ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

የወላይታ ህዝብ ህወሃት ዕድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህጻናትን ለጦርነት የመመልመሉን ተግባር በማውገዝ ለመከላከያ ሰራዊቱ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል።

ከዞኑ ከሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳዳር የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ በመውጣት የአሸባሪውን የህወሃት ትንኮሳ እናከሽፋለን፤ ኢትዮጵያ ከፈተናዎቿ በላይ ሃያል ናት፤ ብሔራዊ ጥቅማችን እና ሉዓላዊነታችን ይከበር፤ እኔ የጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ደጀን ነኝ፤ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ ደማቅ አሻራችን ነው፤ ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች፤ ጦር መሣሪያ ከትግራይ ህፃናት  ትከሻ ይውረድ ፤ክብርና ሞገስ ለመላው የፀጥታ ሀይላችን የሚሉና ሌሎች የተለያዩ መፎክሮችን እያሰሙ እንደሚገኙ ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ህወሓት በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ተብሎ መፈረጁ የሚታወቅ ነው፡፡