የላዳ ታክሲዎችን በአዳዲስ ተሽከርካሪዎች የመተካት ሂደት እየተፋጠነ መሆኑ ተገለጸ

መጋቢት 08/2013 (ዋልታ) – 10ሺህ 500 የላዳ ታክሲዎችን በአዳዲስ ተሽከርካሪዎች የመተካት ሂደት እየተፋጠነ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኤል አውቶ መኪና መገጣጠሚያ ካንፓኒ ከሚገጣጥማቸው 10ሺህ 500 ዘመናዊ ታክሲዎች 500 የሚሆኑትን በመገጣጠም ለባለንብረቶቹና የታክሲ ማህበራት ሰብሳቢዎች በማስጎብኘት መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ የቅኝት ስራዎቹን አካሂዷል፡፡

በቅኝቱም የማህበራቱ አስተባባሪዎች በታክሲዎቹ የአሰራር ሂደት ላይ መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ በሂደቱም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኤል አውቶ የመኪና መገጣጠሚያ ስራ አስፈጻሚ አቶ በቀለ አበበ ምክክሩ የተሻለ መተማመንን የሚፈጥርና ለቀጣይ ስራም አቅም የሚሆን በመሆኑ ጉብኝቱን ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ 10ሺህ 500 ታክሲዎቹን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በአዳዲስ ተሽከርካሪዎች የመተካት ስራ እንደሚጠናቀቅም ተናግረዋል፡፡

(በክብሩ ዋና)