የልማት አጋሮች የአፍሪካን የግብርና ምርቶች ለማሳደግ የ30 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ሊያደርጉ ነው

ጥር 20/2015 (ዋልታ) ዓለም አቀፍ የልማት አጋር ድርጅቶች ለአፍሪካ አህጉር የግብርና ምርቶችን ለማሳደግ የሚውል የ30 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በሴኔጋል ዳካር የተካሄደው 2ኛው የአፍሪካ የምግብ ጉባዔ በትናንትናው ዕለት ተጠናቋል፡፡

በጉባዔው መጠናቀቂያም የልማት አጋሮች የአፍሪካን የግብርና ምርት በማሳደግ አፍሪካ “የዓለም አቀፍ የዳቦ ቅርጫት” እንድትሆን በቅንጅት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ለአፍሪካ የ30 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን የድጋፉን 10 ቢሊዮን ዶላር የአፍሪካ ልማት ባንክ በአምስት ዓመታት ውስጥ ለማዋጣት አቅዷል፡፡

እንዲሁም እስላማዊ ልማት ባንክ 5 ቢሊዮን ዶላር እሰጣለው ብሏል፡፡