የመከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ የሲዳማ ክልል ወጣቶች ሽኝት እየተደረገ ነው

ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ) – የመከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ የሲዳማ ክልል ወጣቶች የሽኝት መርሃ ግብር እየተደረገ ነው፡፡
የመከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል የሀገሪቱን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ ፍቃደኝነታቸውን ለገለፁ ከ4 ሺህ በላይ ወጣቶች ነው የሽኝት መርሃ ግብር እየተከናወነ የሚገኘው፡፡
የክልሉ መንግስት ለመከላከያ ሠራዊት በአይነትና በገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም 300 በግ ፣ 300 ፍየልና 250 በሬ በአጠቃላይ 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ በቀጣይነትም የሚያስፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ክልሉ ዝግጁ መሆኑን ጠቁሟል።