የመከላከያ ሰራዊታችን በሰው ሀይል፤ በአደረጃጀትና በትጥቅ የተሟላ ቁመና ላይ ይገኛል – የመከላከያ ሚኒስትር

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሀም በላይ (ፒኤችዲ)፤ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ባለፋት አመታት በተቋሙ በተሰሩ የሪፎርም ስራዎች በሁለንተናዊ መልኩ የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

ሰራዊቱ በሰው ሀይል፤ በአደረጃጀትና በትጥቅ የተሟላ ቁመና እንዲይዝ ከመደረጉም በላይ ኢትዮጵያን የሚመስል ሰራዊት መገንባት መቻሉንም ገልፀዋል።

ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በጠንካራ ዲሲፒሊን አክባሪነቱ፤ ህዝባዊነቱና ጀግንነቱ ዓለም የመሰከረለት ሰራዊት መሆኑን በተግባር የሀገሩን ሉአላዊነትና ክብር በማስጠበቅ ያስመሰከረ መሆኑንም ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በቀጣይም ሠራዊቱ የሚሰጡትን ማንኛውም ግዳጆች በብቃት ለመወጣት በተሟላ ቁመና ላይ እንደሚገኝም ማረጋገጣቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።