ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 5 ሺሕ 531 ተማሪዎቹን ነገ ያስመርቃል

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርኃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺሕ 531 ተማሪዎቹን ነገ ያስመርቃል።

በዕለቱ በተለያዩ ቅድመ- ምረቃና በድህረ- ምረቃ መርኃ ግብሮች ተምረው ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን እንደሚመረቁም ነው የተገለጸው፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎች፣ ለተመራቂ ቤተሰቦች፣ ለመምህራን እና ለአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በምረቃ ዋዜማው እያስተላለፈም ይገኛል።

የምረቃ ሥነ ሥርዓቱን በዋልታ ቴሌቪዥን በቀጥታ መከታተል እንደሚቻልም ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ደረሰ አማረ (ከጎንደር)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW