የመውሊድ በዓል እየተከበረ ነው 

ጥቅምት 8/2014 (ዋልታ) 1 ሺሕ 496ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት (መውሊድ) በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው።
በዓሉ በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስጅድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች መከበር ጀምሯል።
የመውሊድ በዓል የነቢዩ መሐመድን መልካም ሥራዎች በማሰብና በመተግበር እንዲከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መጠየቁ ይታወሳል።
ዕለቱ የተቸገሩን በመርዳት እንዲያልፍና መተጋገዙም የሰርክ ተግባር እንዲሆን ነው የተጠየቀው።
ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም በዓልን ይመኛል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!