የሶማሌ ክልል መንግሥት ምስረታ ተካሄደ

ጥቅምት 8/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የአዲሱን መንግሥት ምስረታ ጉባኤ በጅጅጋ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።
መስከረም 20 በክልሉ የተካሄደውን 6ኛው አገር ዐቀፍ ምርጫ ተከትሎ ነው በክልሉ ርዕሰ ከተማ ጅግጅጋ ከተማ አዲሱ የክልሉ ምክር ቤት የሚመሰረተውና መንግሥትንም የሚያዋቅረው።
272 መቀመጫዎች ያለው የክልሉ የምክር ቤት መስራች ጉባኤ የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ ይመርጣል።
ምክር ቤቱ በክልሉ ብልፅግና ፓርቲ የሚቀርበውን ዕጩ በርዕሰ መስተዳድርነት የሚሰይምም ይሆናል።
የክልሉን አዲስ መንግሥት ምስረታ ለመታደም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የተገኙ ሲሆን፤ በሶማሌላንድ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱረህማን አብዱላሂ ሰይሊኢ የተመራ ልዑክ ትናንት ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ መግባቱን መዘገባችንም ይታወሳል።
በሱራፌል መንግሥቴ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!