የሚሲዮን መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባና ስልጠና መካሄድ ጀመረ

ታኅሣሥ 17/2015 (ዋልታ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችና የሚሲዮን መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባና ስልጠና መካሄድ ጀምሯል።

ስብሰባው በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ነው በዛሬው ዕለት የተጀመረው።

ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የወከሉ ሚሲዮኖች፣ ምክትል ሚሲዮኖች እንዲሁም ዳይሬክተር ጀነራሎች ተሳታፊ መሆናቸውም ተገልጿል።

በዓመታዊ ስብሰባና ስልጠና መክፈቻ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታዎች ተገኝተዋል።

ዓመታዊው ስብሰባና ስልጠና ከዛሬ ታኅሣሥ 14 እስከ 27/2015 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

በሰለሞን በየነ