የማዕድን ኤክስፖን በመጀመሪያው ቀን ከ10 ሺሕ በላይ ሰዎች መጎብኘታቸው ተገለጸ

የማዕድን ኤክስፖ

ኅዳር 2/2015 (ዋልታ) በትናንትናው ዕለት የተከፈተው የማዕድን ኤክስፖ በመጀመሪያው ቀን ብቻ ከ10 ሺሕ በላይ ጎብኝዎችን ማስተናገዱን የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ዑማ ገለጹ።

ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ዛሬም በሚሊኒየም አዳራሽ በመገኘት የሀገሪቱን ሀብት ለማወቅ ኤክስፖውን የሚታደሙትን እንግዶች ለማስተናገድ ዝግጁ ነን ብለዋል።

ነገ ኅዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም የማዕድን ኢንዱስትሪ አምራች ባለቤቶች፣ ዋና ሥራ አስፈፃዎች እንዲሁም ቴክኖሎጂ እና ፋይናንስ አቅራቢዎች በተዘጋጀው የፓናል ውይይት እጅግ ጠቃሚ ሐሳብ እንደሚያቀርቡም ጠቁመዋል። ፍላጎቱ ያላቸው ሁሉ በውይይቱ እንዲሳተፉም ሚኒስትሩ ግብዣ አቅርበዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW