የዩኒቨርሲቲዎች የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ አየተካደ ነው


ሐምሌ 26/2013 (ዋልታ) – የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው የተለዩ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች የተገኙበት የውይይት መድረክ ላይ የ2014 የትኩረት አቅጣጫዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዩኒቨርሲቲዎች በእቅዶቻቸው መሰረት ወደ ልህቀት እንዲያመሩ የሚያስችሏቸው ሀሳቦችም በግብአትነት መልክ ይወሰዳሉ ተብሏል።

ዕቅዱ የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴርን የትኩረት አቅጣጫ ያካተቱ ስለመሆናቸው፣መስፈርቱን ያሟሉ መሆናቸው እና ተቀባይነት ያላቸው ስለመሆኑ ግምገማ ማካሄድን ዓላማው አድርጓል።

የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርትም ቀርቧል።

(በትእግስት ዘላለም)