አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉና አትሌት ለምለም ኃይሉ በ1500 ሜትር ለግማሽ ፍጻሜ ደረሱ

ሐምሌ 26/2013 (ዋልታ) – አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ እና አትሌት ለምለም ኃይሉ በ1500 ሜትር  ለግማሽ ፍጻሜ ደርሰዋል፡፡

በሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ በሶስት የተለያየ ምደብ ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ተወዳዳሪ አትሌቶቻችን መካከል ሁለቱ የመጀመሪያውን ዙር ማጣሪያ አልፈዋል።

አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ  እና አትሌት ለምለም ኃይሉ  ከየምድባቸው 5ኛ ደረጃን በመያዝ ለቀጣዩ የርቀቱ ግማሽ ፍፃሜ የተቀላቀሉ አትሌቶች ናቸው።

ለግማሽ ፍጻሜ ያለፋት አትሌቶች  ውድድራቸውን ረቡዕ እኩለ ቀን ላይ ያደርጋሉ።

ነገር ግን በሌላኛው ምድብ ውድድሯን ያደረገችው አትሌት ድርቤ ወልተጂ ደግሞ የመጀመሪያውን ዙር ማጣሪያ  ሳታልፍ መቅረቷን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።