የምክር ቤት አባል የነበሩት ሻለቃ መኮንን ገለታ አረፉ

ጥቅምት 03/2014 (ዋልታ) – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ሻለቃ መኮንን ገለታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ሻለቃ መኮንን ገለታ ማሩ በ3ኛ ዙር አገራዊ ምርጫ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን በኮምቦልቻ ምርጫ ክልል የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ኅብረትን (ኢዴኃኅ) በመወከል ተመርጠው የሕዝብ ተወከዮች ምክር ቤት አባል በመሆን ሕዝባቸውን በታማኝነትና በቅንነት አገልግለዋል፡፡

ሻለቃ መኮንን ገለታ ከ1970 እስከ 1983 በአገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎችም አገልግለዋል፡፡

ሻለቃ መኮንን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ስረዱ ቆይተው በተወለዱ በ65 ዓመታቸው ጥቅምት 3/2014 ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡