የምዕራብና ሰሜን ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

የምዕራብና ሰሜን ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

የምዕራብና ሰሜን ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የጋራ የምክክር መድረክ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

 

በምክክር መድረኩ ላይ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳደሮች አፈጉባኤዎችና ጉዳዪ የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል ስራ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

 

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ በህዝቦች መካከል በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር ሁሉም ክልሎች ተባብረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

 

ሌላው በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በክልሎች መሀል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ህልውናን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

 

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም እንደዚህ አይነት መሰል መድረኮች እርስ በእርስ ተገናኝተን ችግራችንን እንድንቀርፍና ለሀገር አንድነት እንድንሰራ የሚያደርግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።