የሰንደቅ ዓላማ ቀን ስናከብር ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይላት አንገታቸውን የሚደፉበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ነው- አቶ ደመቀ መኮንን

አቶ ደመቀ መኮንን

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) የሰንደቅ ዓላማ ቀን ስናከብር ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይላት አንገታቸውን የሚደፉበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል 14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲያከብሩ ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ሰንደቅ ዓላማ ክብር በየተሰማራበት የሥራ መስክ ታላቅ ስኬት ማስመዝገብ ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በወታደራዊ ካምፖች፣ ኤምባሲዎች እና በሌሎች ተቋማት እየተከበረ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።