የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ድጋፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች

መስከረም 14/2014 (ዋልታ) የሰዎች ለሰዎች ድርጅት በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ምክንያት ከሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደሴ ለተጠለሉ ወገኖች ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና የአልባሳት ቁሳቁስ ድጋፍ አደርጓል።
ድርጅቱ በኢትዮጵያ ላለፉት 40 ዓመታት በተለያዩ የልማት ስራዎችን ሲስራ ቆይቷል።
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ ይልማ ታየ ድርጅቱ በመሰረተ ልማት ስራ ላይ የተሰማራ ቢሆንም ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መውደቅ ስለሌለባቸው የተለያዩ ቁሳቁስን ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።
ድጋፉ የመጀመሪያ ቢሆንም በቀጣይም ድርጅቱ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አሁን የምናተርፍበት ወቅት ሳይሆን የምንሻገርበት ጊዜ ነው ብሏል።
ሁሉም ሀገር ከገባችበት ፈተና እንድትሻገር መስራት እንደሚገባም ገልጿል።
በሳራ ስዩም
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!