የሱዳን ኤሌክትሪክ ኩባንያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) – በሱዳን ኤሌክትሪክ ኩባንያ (ሱዳን ኤሌክትሪክ ትራንስሚሽን ኮርፖሬሽን) ዋና ሥራ አስፈጻሚ የቴክኒክ አማካሪ የተመራ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

በኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አህመድ አደም ኡመር የተመራውና አምስት አባላትን ያካተተው ልዑክ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስትራቴጂና ኢንቨስትመንት መምሪያ ዳይሬክተር ወንድወሰን ተሾመ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ልዑክ ቡድኑ በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል በቀጣይ ስለሚኖረው የኃይል ትስስር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚመክር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ምክክሩ ከጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ተመላክቷል፡፡