የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ለሠራዊቱ ድጋፍ አደረጉ

ነሀሴ 24/2013 (ዋልታ) – የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

ሚኒስትሩ ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ጨምሮ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ማህበረሰብ ለሰራዊቱ ደም መለገሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ዶክተር ሳሙኤል  ፤በዱር ገደሉ ለሀገራችን ሉዓለዊነት የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊቱ ደማችንን በመለገሳችን ኩራት ይሰማናል  ሲሉ ገልጸዋል።