የስራ እድል ፈጠራ በእውቀት ላይ የተመረኮዘ መሆን እንዳለበት ተገለፀ

ግንቦት 23/2013 (ዋልታ) – የስራ እድል ፈጠራ በእውቀት ላይ የተመረኮዘ መሆን እንዳለበት ተገለፀ፡፡
እስካሁን በኢትዮጵያ በነበሩ የስራ እድል ፈጠራ ውስጥ የትምህርት የክህሎት እና የመረጃ ፍሰት የዘርፉ ትልቁ ችግር እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የስራ እድል ፈጠራ አማካሪ ምክር ቤት ሶስተኛዉን ኮንፍረንስ ያካሄደ ሲሆን ምክር ቤቱ በዘርፉ ያዳረጋቸዉን ጥናቶች ይፋ አድርጓል፡፡ በጥናቱም መሰረት ዘላቂ እና የተረጋጋ የስራ እድል ለመፍጠር የሚይስችሉ አቅጣጫዎችን የሚጦቁም ነው ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ እስከ 2020 ዓ.ም ከ20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ እና የተረጋጋ የስራ እድል ለመፍጠር እየሰራች ትገኛለች፣ ታድያ ይህ እንዲሳካ በእውቀት ላይ የተመሰረተ መሆን እዳለበት ነው የተገለፀው፡፡ የስራ እድል ፈጠራ አማካሪ ምክር ቤት ባካሄደው ሶስተኛው ኮንፍረንስ ላይ በሀገሪቷ ባሉ የስራ እድል ፈጠራ ውስጥ ሶስት ዋና ችግሮች መኖራቸዉን መለየቱን አስታውቋል፡፡
በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ታድያ ጥናት እና ምርምር አስፈላጊ በመሆናቸው ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
(በሚልኪያስ አዱኛ)