የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተወያዩ

ጥር 3/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አዲሱን የአገር መከላከያ ዋና መስሪያ ቤትን በመጎብኘት ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተወያዩ።
በጉብኝቱ ላይ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ፣ የልዩ ኃይል አዛዥ፣ የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
በውይይታቸው በአፍሪካ ቀንድ እንቅስቃሴ፣ በአገሪቱ እና በክልሉ ስላለው የጸጥታ ጉዳይ ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውን የክልሉ የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ መግለጻቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።