የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ያስገነባው የረገ ኤያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

ሰኔ 4/2014 (ዋልታ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስገነባው የረገ ኤያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ መሀመድ ጀማል እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ትምህርት ቤቱ በውስጡ 10 መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-ሙከራ፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ የተማሪ ክሊኒክ፣ የአስተዳደር ሕንጻና የስብሰባ አዳራሽ ያካተተ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

የቀዳማዊ እመቤት ጽሕፈት ቤት ከዚህ ቀደም በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ማመዴ ቀበሌ ሁለተኛው ትምህርት ቤት አስገንብቶ ማስመረቁ የሚታወስ ነው።