የቀጠለው የም/ጠ/ሚ/ር ደመቀ የተናጠል ውይይት

ደመቀ መኮንን ከጋቦን የው/ጉ/ሚ ፓኮሜ ሞቤሌት ቡቤያ ጋር

መስከረም 12/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጋቦን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓኮሜ ሞቤሌት ቡቤያ ጋር በኒውዮርክ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ የኢትዮጵያ እና ጋቦን የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ተነስተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቅርቡ ጋቦን በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ቀጣይ አባል መሆኗን ተከትሎ፤ ለአፍሪካውያን ድምፅ በመሆን ሚናዋን እንደምትወጣ ያላቸውን ዕምነት ገልፀዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ ቀንድ ያለው ትኩረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በመጥቀስ፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካውያን መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በአፅንኦት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እና ጋቦን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ደመቀ መኮንን ከዩኤኢ የሼክ አህመድ ቢን አህመድ አሊ ጋር

በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ አህመድ ቢን አህመድ አሊ ጋር በኒውዮርክ ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።