የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ኮምፒውተሮችና ፕሪንተሮችን ለትግራይ ክልል ድጋፍ አደረገ

የካቲት 16/2013 (ዋልታ) – የቂርቆስ ክፍለ ከተማ በጁንታው ዘረፋ ለደረሰባቸው የመንግስት ተቋማት ይሆን ዘንድ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው ኮምፒውተሮችና ፕሪንተሮችን ለትግራይ ክልል ድጋፍ አድርጓል፡፡

በትግራይ ክልል በጁንታው ዘረፋና ውድመት ያጋጠማቸውን የመንግስት ተቋማት መልሶ ለማደራጀት ተግባር ይውሉ ዘንድ የክፍለ ከተማው አስተዳደር የ47 ኮምፒውተሮች 17 ፕሪንተሮች ድጋፍ ማድረጉን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል ረዲ ተናግረዋል፡፡

“ኢትዮጵያ በተባበረ ክንድ ብልፅግናዋን ታረጋግጣለች፤ ትግራይም ከገጠማት ጊዜያዊ ችግር ተላቃ ለነዋሪዎቿ ምቹ ክልል ትሆናለች” ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚው፡፡

ኮምፒውተሮቹና ፕሪንተሮቹ 2 ሚሊዮን 219 ሺህ ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡