የቡድን 20 ሀገራት የብድር ውሳኔ ተገቢነት

መስከረም 12/2014 (ዋልታ) የገንዘብ ሚኒስቴር የቡድን 20 ሀገራት የብድር ኮሚቴ በአውሮፓዊያኑ መስከረም 16 ስብሰባው የዕዳ ማቃለል በወቅቱ ማድረግ እንዲቻል የወሰደውን እርምጃ አስፈላጊ እና ኢትዮጵያ በደስታ የምትቀበለው መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አበዳሪ ኮሚቴው የብድር ማቃለሉ ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚው ፍላጎት ጋር ተጣጥሞ ሂደቱን ለማቀላጠፍ በሚያደርገው ጥረት ባሳየው ቁርጠኝነት ደስተኞች ነን ብሏል በመግለጫው፡፡

የኮሚቴው እርምጃ የሀገሪቱን የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት ለማረጋገጥ እንደ መሰረታዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተጠቅሷል፡፡

በዚህም ለአበዳሪ ኮሚቴው የጋራ ሊቀመንበሮች እስካሁን ለሠሩት ሥራ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

በተለይ ፈረንሣይ እና የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ በጋራ ሆነው ኮሚቴውን ለማቋቋም ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት እና በስብሰባው ላይ ለመገኘት እና ጥያቄውን ለማቅረብ ላደረጉት እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግሥት እውቅና ይሰጣል ነው ያለው ሚኒስቴሩ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አዲሱን የኢኮኖሚ ሪፎርም ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግና ለውጡ ውጤታማ እንዲሆን ቁርጠኛ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ የተሃድሶ ሂደት ላደረገው የተራዘመ የብድር አከፋፈል መርሃ ግብር ድጋፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እውቅና መስጠቱን ጠቅሷል፡፡

መንግስት ጊዜው ያለፈበትን ብድር እንዲሁም በአዲስ በሚገኘው ብድር ለድህነት ቅነሳ እና የእድገት መሰረት እንዲሆን የሚያስችል የብድር ተቋሙን ዝግጅት መጠየቁን የገንዘብ ሚኒስቴር በመግለጫው ማስታወቁን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡