የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እርዳታ አደረገ

ሐምሌ 9 ቀን 2013 (ዋልታ) – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለጌርጌሴኖን አእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በእሳት አደጋ ምክንያት ሀብት ንብረታቸውን አጥተው በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ  ለሚገኙ ተጎጂዎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ የተደረገው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው እና የባህል ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ብዙነሸ መሰረት በተገኙበት ነው፡፡

በዚሁ ወቅት ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደተናገሩት ÷ ይህን መሰል የድጋፍ ስራዎች የአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት የሚቀጥል ነው።

አያይዘውም እንደነዚህ ያሉ የበጎ አድራጎት ስራዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ሊበረታቱ ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።