የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪ ማዕከል ዘርፈ ብዙ ምላሽ ሰጪ የሚኒስትሮች ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል

የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪ ማዕከል ዘርፈ ብዙ ምላሽ ሰጪ የሚኒስትሮች ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

ኮሚቴው በትግራይ ክልል በህግ ማስከበር ሂደቱ ለተከሰቱ ሰብዓዊና ማህበራዊ ቀውሶች ምላሽ አሰጣጥ ተግባራትን እንዲሁም የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ላይ ነው ውይይት ያካሄደው፡፡

በሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትና ስርጭት እንዲሁም የመልሶ ማቋቋም ሂደት ዙሪያ በየዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም የየዘርፍ ሪፖርት ቀርቧል።

በተጨማሪም የማዕከሉንና የየዘርፍ ባለድርሻ አካላትን የተግባር እንቅስቃሴ እንዲሁም የሰብዓዊ ድጋፍ እና እየተካሄደ ያለውን የመልሶ ማቋቋም ሂደት ከዕቅድ ጀምሮ አሁን ያለበትን ደረጃ የሚዳስስ ጽሁፍ ቀርቧል፡፡

በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጎ የስርጭት አቅርቦትን ለማሳደግና የቅድሚያ  የሚሰጣቸው ተግባራት መለየቱ ተገልጿል፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል አፋጣኝ ምላሽ መስጠቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበው፣ የቀጣይ ተግባራት መመሪያ መስጠታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።