የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ሠራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለገሱ

ሐምሌ 30/2013 (ዋልታ) – የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለገሱ፡፡
የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ለቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ነው የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ለመስጠት የወሰኑት ፡፡
በጽህፈት ቤቱ የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከመስጠት ባለፈ የደም ልገሳ ለማድረግ መወሰናቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም የጽህፈት ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ግንባር ድረስ በመሄድ ሰራዊቱን በማንኛውም መልኩ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡