የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ተጀመረ

የካቲት 1/2014 (ዋልታ) የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ መድረክ ሥልጠና ተጀምሯል፡፡

የአቅም ግንባታ መድረኩ ዓላማ አመራሩ ወቅቱ የሚጠይቀውን የአመራር ብቃትና አስተሳሰብ እንዲያጎለብትና የመረጠውን ሕዝብ በትጋትና በቅንነት እንዲያገለግል ለማስቻል ነው ተብሏል።

መድረኩ ጥንካሬዎችንና መልካም አፈጻጸሞችን አጠናክሮ በማስቀጠል የታዩ ውስንነቶችን ደግም ነቅሶ በማረም ሕዝቡ በሚጠብቀው ደረጃ ለማገልገል የሚያስችል የአመራር አቅም ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።

በሥልጠናው ከ320 በላይ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎችን ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች ይሳተፋሉ፡፡

ሥልጠናው ለሚቀጥሉት አራት ቀናት የሚቆይ መሆኑን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡