የብሔራዊ መታወቂያ ስርዓት የመጀመሪያ ሙከራ ተጠናቀቀ

የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – የብሔራዊ መታወቂያ ስርዓት “አንድ ሰው አንድ ነው” በሚል መሪ ሃሳብ የመጀመሪያውን የቅድመ ትግበራ ሙከራ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የሰላም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የብሔራዊ መታወቂያ ስርዓትን የማወቀርና በበላይነት የመምራት ተግባሩን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግና የእያንዳንዱን ዜጋና ነዋሪ ማንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመለየት የሚያስችል በአገር አቀፍ ደረጃ ስርዓት ዘርግቶ እየሰራ ይገኛል።

በቴክኖሎጂ የታገዘው የብሔራዊ መታወቂያ ስርአት መሰረታዊ መረጃዎችን እንዲሁም የባዮሜትሪክ ዳታ (ፎቶ ግራፍ፣ የአስሩም ጣት አሻራና የአይን ብሌን) የሚያካትት መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ ስርአት የአንድ ሰው ማንነት የሚረጋገጠው በካርድ ብቻ ሳይሆን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በታገዘ የባዮሜትሪክ ስርዓት በመሆኑ በማስመሰል የሚደረጉ የተለያዩ ማጭበርበሮችን በአስተማማኝነት መከላከል የሚያስችል መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገነው መረጃ አመላክቷል፡፡