የተረጋጋች ኢትዮጵያን ማየት የሁላችንም ህልም ነው ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ገለጹ

መጋቢት 2/2014 (ዋልታ) በአገራችን ሰላም ሰፍኖ የተረጋጋች ኢትዮጵያን እውን ሆና ማየት የሁላችንም ህልም ነው ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ራሄል ባፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ራሄል ባፌ (ዶ/ር) ይህንን ያሉት ብልፅግና ፓርቲ እያካሄደ በሚገኘው አንደኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

ከትላንታችን የሚበልጥ ነገን ማየት ከቻልን ዓለምን ማነጋገር የሚያስችል ለውጥ ማምጣት እንደሚቻልም ተናግረዋል፡፡

በአገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና የጎላ እንደሆነ የጠቆሙት ሰብሳቢዋ  አገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በሱራፌል መንግሥቴ