ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃን ወቅታዊ የማድረጊያ ቀነ ገደብ ለሁለት ወራት መራዘሙን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

መጋቢት 2/2014 (ዋልታ) በተለያዩ ምክንያቶች መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ላልቻሉ ደንበኞች ተጨማሪ የሁለት ወር ጊዜ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ፡፡

በዚህም ደንበኞች ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች በመሄድ መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ በ27/08/2021 ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ ላለፉት 6 ወራት የደንበኞቹን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ሥራ ሲሠራ መቆየቱን አስታውሶ በዚህ ጊዜ ውስጥ በርካታ ደንበኞች መረጃቸውን በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወቅታዊ ማድረጋቸውን አመልክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW