የተቋማዊ መዋቅር ለውጥ ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ

ታኅሣሥ 21/2014 (ዋልታ)አገራዊ፣ ክፍለ አኅጉራዊ እንዲሁም ዓለም ዐቀፋዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ተቋማዊ የመዋቅር ለውጥ ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ባሳለፈው ሳምንት የ100 ቀን አፈጻጸም ግምገማ ማካሄዱን በመግለጽ ተቋማዊ ለውጡ ስኬታማ መሆኑን ጠቋሚ እንደሆነ ነው ያነሱት፡፡

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሸባሪው ትሕነግ ነፃ በወጡ አካባቢዎች ጉብኝትን በተመለከተ መልሶ በማቋቋም ረገድ አገራዊ ጥሪ ማቅረባቸውን አምባሳደር ዲና አስታውሰዋል፡፡

ወደ አገር ቤት እየገቡ የሚገኙ ዲያስፖራዎችን በተመለከም ያሳየው መነሳሳት ከመንግሥት ምስጋና የቀረበበት ነው ብለዋል፡፡

ለዲያስፖራው ማኅበረሰብ ዲፕሎማሲያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ጨምሮ በርካታ መርሃ ግብሮች መዘጋጀታቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በሰለሞን በየነ