የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ

መጋቢት 30/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሰብሳቢነት የሚመሩት የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ስብሳባ ዛሬ ተካሂዷል፡፡

በስበሰባው የውሃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን የደቡብ፣ የደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች፣ የጋምቤላ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች የተገኙ ሲሆን የቀሪ ክልሎች የውሃ ቢሮ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ክልላቸውን በመወከል ስብሰባውን ተሳትፈዋል፡፡

የመስኖና ቆላማ አከባቢዎችና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሮች እንዲሁም የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እና ሌሎች ባለድርሻዎች ጭምር በስበሰባው ላይ መገኘታቸውን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በስብሰባው ባሳለፍነው የ2013 ዓ.ም የተሰሩ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች፣ ቅድመ ጎርፍ መከላከል፣ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች ፣ እንቦጭ መከላከል እና የተፋሰስ እቅዶችንና የተፋሰሶች ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል፡፡