የትምህርት ሚኒስቴር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊየን ማቲዮስ የትምህርት መርሀግብሩን ለማስቀጠል የሀገር ሰላም ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ የመከላከያ ሰራዊቱ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ ያደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስቴርም እንደ ተቋም መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን እና በቀጣይም ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን እንደሚቆም አስታውቀዋል።

የገንዘብ ስጦታውን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሊዊጂ ትምህርት ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከዚህ ቀደም “ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ደም መለገሳቸው ይታወሳል።