የትምህርት ሚኒስትሩ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄዱ

መስከረም 28/2014 (ዋልታ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ሰራተኛ ጋር በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዬች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም ሰራተኛው በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ አሉ ያለቱን የአሰራር ፣ የመልካም አስተዳደር  እና የአደረጃጀት ችግሮች  ለሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በቀጣይም ሚኒስትሩ በተቋም ውስጥ ያሉትን ችግሮች በመፈተሽ መፍትሄ  የመስጠት  እና የትምህርት ሴክተሩን ከ ፓለቲካ እና ከ ንግድ ነፃ ለማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ ሰራተኞቹ  ገልፀዋል።

ሚኒስትሩም በሰራተኞች የተነሱትን ሀሳቦች እንደ ግብዓት በመውሰድ እና መፍትሄ በመስጠት በቅንጅት የተሻለ ስራዎችን  ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የትምህርት ሴክተሩ የፓለቲካ መስሪያ ቤት ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል የተቋቋመ ሴክተር በመሆኑ የፓሊቲካ አመለካከታችንን ትተን  ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በቀጣይም ሚኒስትሪው የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር  ከፍተኛ ሀላፊነት ያለበት ተቋም በመሆኑ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚጠበቅም ገልፀዋል።