የትግራይ ወጣቶች በህወሓት የሚደርስባቸውን ግፍና በደል እየሸሹ ለሰራዊቱ እጃቸውን እየሰጡ ነው

ነሐሴ 23/2013 (ዋልታ) – የትግራይ ወጣቶች በአሸባሪው ህወሓት የሚደርስባቸውን ግፍና በደል እየሸሹ ለአገር መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ ነው::

ግርማይ ቴዎድሮስና ወጣት ጎይቶም ሀዱሽ የአድአሮይና እንዳአባጎና አካባቢ ነዋሪዎች ናቸው።

የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከዕለታት አንድ ቀን  ወጣቶቹን ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር አስገድዶ ወደ ጦር ሜዳ እንደወሰዳቸው ይናገራሉ።

ከተወሰዱም በኋላም ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን የተለያዩ የጦር መሣሪያ እንዲያደርሱና ቁስለኛ እንዲያመላልሱ የሥራ ድርሻ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

ይህን ሲያደርጉም በቀን አንድ ኮቾሮ ያለ ውሃ እየተሰጣቸው በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሳለፉ ይገልፃሉ።

ወጣቶቹ እንደሚሉት በትግራይ አንድ ቤተስብ ከሚሰጠው የዕርዳታ እህል ግማሹን ለአሸባሪው ቡድን የመስጠት ግደታ አለበት።

በዚህም በትግራይ ክልል ዜጎች በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከፍተኛ ግፍና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ግፍና በደል ያስመረራቸው እነዚህ ወጣቶች ከሚኖሩበት ካምፕ በድብቅ አምልጠው ለአገር መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን ሰጥተዋለ።

ወጣቶቹ እጃቸውን ከሰጡ በኋላ ሰራዊቱ ድጋፍና እንክብካቤ እያደረገላቸው እንደሆነ ገልፀዋል።