ጠ/ሚ ዐቢይ በሩዋንዳ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቀረቡ

ነሀሴ 23/2013 (ዋልታ) – ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሩዋንዳ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ለእኔ እና ለልዑካን ቡድኔ ስላደረጉት ደማቅ አቀባበል ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜን አመሰግናለሁ” ብለዋል፡፡

በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መልካም ውይይት ማካሄዳቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልፀዋል፡፡