የቻን አፍሪካ ዋንጫ ዛሬ በይፋ ይጀመራል

የቻን አፍሪካ ዋንጫ

ጥር 5/2015 (ዋልታ) የቻን አፍሪካ ዋንጫ ዛሬ በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በይፋ ይጀምራል፡፡

17 ሀገራት የሚሳተፉበት ይህ ውድድር በአራት ከተሞች በሚገኙ ስታዲየሞች ይከናወናልም ነው የተባለው፡፡

አልጄሪያ ለዚህ ውድድር ያስገነባችው የኔልሰን ማንዴላ ስታዲየም ትላንት በይፋ የተመረቀ ሲሆን ዛሬ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያስተናግዳል፡፡

በመክፈቻው የውድድሩ አዘጋጅ አልጄሪያ ከሊቢያ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡

በዚህ ምድብ የምትገኘው ኢትዮጵያ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ከሞዛምቢክ ጋር ጨዋታዋን ታከናውናለች፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በጨዋታው ለመሳተፍ ወደ አልጄሪያ ባሳለፍነው ረቡዕ ያቀና ሲሆን ትላንት የመጀመሪያ ልምምዱን አከናውኗል፡፡

ዋልያዎቹ ከዚህ ቀደም በ2014 እና 2016 በቻን አፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉ ሲሆን ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ በውበቱ አባተ እየተመሩ በመድረኩ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

በሀብታሙ ገደቤ