የናይጀሪያ መንግሥት ልዑካን ቡድን ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እየጎበኘ ነው

የካቲት 1/2014 (ዋልታ) በተቀናጀ የአግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ኢትዮጵያ የገባው የናይጀሪያ መንግሥት ልዑካን ቡድን አባላት አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እየጎበኘ ይገኛል፡፡

በናይጄሪያ የግብርና ሚኒስትር ሙሃመድ ማሃሙድ አቡበከር የተመራው 7 የግዛት አስተዳደር ኃላፊዎችን ጨምሮ 30 አባላት ያሉት ልዑኩ በዛሬው ዕለት የይርጋለም አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክን ይጎበኛሉ፡፡

የልዑኩ በትላንትናው ዕለት ቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን መጎብኘታቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡