የኛ- ሆም የተሰኘ የድረ-ገፅ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – “ከቤትዎ ውጪ ልክ እንደ ቤትዎ” በሚል የኛ- ሆም የተሰኘ የድረ ገፅ መተግበሪያ ይፋ ሆነ።
መተግበሪያው ደረጃውን የጠበቀ ሆቴልና እንግዳ ማረፊያ ቦታ የሚፈልጉ እንግዶችን ማስተናገድ የሚያስችል ቴክኞሎጂ እንደሆነ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሆቴልና የእንግዳ ማረፊያ አገልግሎት በዘመናዊና በተቀላጠፈ መልኩ አስተማማኝነትን በማከል ቴክኖሎጂ በመታገዝ በሞባይል መተግበሪያ የአለም አቀፍና ሀገር ውስጥ የማህበረሰብ ክፍሎች ማስተናገድ ያስችላል ነው የተባለው።
እንግዳ ተቀባይ መካከል ያለውን አካላዊ ርቀትና መልካምድራዊ የገበያ ርቀት ቴክኖሎጂ በመታገዝ የእንግዳ ማረፊያ ሀሳብን እንዲሁም አጠቃላይ መስተንግዶ ለማቃለል ታስቦ የተሰራ የኢትዮጵያ ድረ-ገፅ መተግበሪያ እንደሆነም ተመላክቷል።
የኛ ሆም የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሻሻል የተነሳ ድርጅት መሆኑም ተገልጿል።
(በሃኒ አበበ)