የአማራ ክልል ባለ ሃብቶች ለመከላከያ ሠራዊት 1.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

ነሀሴ 24/2013 (ዋልታ) – የአማራ ክልል ባለ ሃብቶች በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኙት የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ 1ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የአልባሳት እና የለስላሳ መጠጦች ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉ 150 ደርዘን የለስላሳ መጠጥ ፣ 150 የውሀ ኮዳ እና 1ሺ 500 ካነቴራ ነው።
የባለሀብቶቹ ተወካይ አቶ ሙሉጌታ ቢያዝን እንደተናገሩት ፣ ይህ ድጋፍ በሀገር ውስጥ ባሉ የአማራ ባለሀብቶች ብቻ የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀው ፤ በቀጣይ በውጪ ሀገር ከሚኖሩ ባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት አሸባሪው የህውሓት ቡድን ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰስ ድረስ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የምዕራብ ዕዝ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል የሎጅስቲክ አስተባባሪ ሻ/ቃ ጉልላት ነጋሽ፣ በአማራ ክልል የሚገኙ ባለ ሀብቶች ለፀጥታ ሃይሉ ላደረኩት ድጋፍ ማመስገናቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡