የአሸባሪውን ሴራ ያጋለጠችው የትግራይ ተወላጇ የሲቢኤስ ጋዜጠኛ

መስከረም 14/2014 (ዋልታ) “የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት ጥሩ ሆኖ እንዳይታይ የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ለትግራይ ሕዝብ ሰብኣዊ ድጋፍ ኢንዲደርስ አይፈልግም” ስትል  የቡድኑን ሴራ ያጋለጠችው የሲቢኤስ ጋዜጠኛዋ ኢትዮ-አሜሪካዊት ሔርሜላ አረጋዊ እውነትን በመግለጿ ከአሸባሪው ደጋፊዎች ተቃውሞን እያስተናገደች ነው፡፡

ታዋቂዋ ኢትዮ-አሜሪካዊት የትግራይ ተወላጅ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ በትዊተር ገጿ አሸባሪው ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ ለሥልጣን ጥቅሙ ሲል እየተጠቀመበት መሆኑን አስፍራለች፡፡

መንግሥት የሽብር ቡድኑ ረሃብን እንደ ጦርነት መሳሪያ እየተጠቀመ እንደሆነና ሰብኣዊ አቅርቦት በሚታሰበው ልክ እንዳይደርስ እንቅፋት ስለመፍጠሩ በተደጋጋሚ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ጋዜጠኛዋ በጽሑፏ በዲያስፖራው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ቢሰበሰብም በትግራይ ላሉት ድሆች አለመድረሱን ታነሳና ታዲያ ገንዘቡ ጦርነቱን ለመደገፍ እየዋለ ነውን? ስትል ትጠይቃለች፡፡

“ባለፉት 10 በላይ ወራት በትግራይ ተከሰተ የተባለውና የሰማሁት ነገር አይመጣጠንም አሁንም ነገሮችን በተለየ ዓይን በመመልከት ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ እናምጣ” ስትል አሳስባለች፡፡

አሸባሪው ሕወሓት በከፈተው ጦርነት በትግራይ በርካታ ንጹሃን እንደተገደሉ አይተናል የምትለው ጋዜጠኛዋ ጥያቄ ውስጥ መግባት ባለበት ጦርነትስ ምንያክል አዳጊ ወታደሮች ተገድለው ይሆን? የሚል ጥያቄንም ታስከትላለች፡፡ በመሆኑም የትግራይ ተወላጅ ዲያስፖራዎች በጭፍን ከደመደገፍ ታቅበው ማሰብ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርባለች፡፡