የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ እጣ ድልድል ይፋ ሆነ

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የጥሎ ማለፍ  የእጣ ድልድል  ዛሬ ከሰዓት ይፋ ተደርጓል።

16 ቡድኖች እርስ በርስ በሚፋለሙበት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ውድድር የአምናው አሸናፊ ባየር ሙኒክ ከላዚዮ ተደልድሏል።

ከባድ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ  የሚጠበቀው ሌላ ጨዋታ ባርሴሎና ከፓሪስሰንት ጀርሜን የሚገናኙበት ሆኗል።

የሁለት ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ አትሌቲኮ ማድሪድ ቼልሲን የሚገጥምበት ሌላኛው ተጠባቂ ፍልሚያ ነው።

እንዲሁም ማንችስተር ዩናይትድን ከውድድሩ ያሰናበተው የጀርመኑ አርቢ ላይብዚግ ሌላኛውን የእንግሊዝ ክለብ ከሊቨርፑል ጋር ይፋጠጣል።

አምና እስከ ግማሽ ፍጻሜ ድረስ  መጓዝ የቻለው የጀርመኑ ክለብ እ.አ.ኤ 2019 የውድድሩ አሸናፊ የነበረው ሊቨርፑልን ይፈትነዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በምድብ ጨዋታዎች ከውድድሩ ሊሰናበት ተቃርቦ የነበረው እና የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግን ለ13 ጊዜያት ያክል ያሸነፈው ሪያል ማድሪድ ከአታላንታ ጋር  ይጫወታል።

ቦሩሲያ ሞንቼግላድባህ ከማንችስተር ሲቲ እና ሴቪያ ከቦሩሲያ ዶርትሞንድ ደግሞ ሌሎች  የግማሽ ፍጻሜ  ጨዋታዎች መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።