የትግራይ ክልል የአየር መሥመር ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደትን ተከትሎ ተዘግቶ የነበረው የአየር ክልል ከዛሬ ታህሣሥ 05/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ክፍት መሆኑ ተገለጸ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የአለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ነው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ያስታወቀው፡፡

በመስመሩ ላይ አገልግሎት መሥጠት የሚችሉ ኤርፖርቶች በረራ ማስተናገድ የሚችሉ መሆኑንም ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡