የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ያካሂዳል

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት

ሐምሌ 10/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት 3ኛውን መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ የበጀት አመቱ የማጠቃለያ ሪፖርት በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩን የኦዲት ሪፖርት ለምክር ቤት የሚቀርብ ሲሆን፣ የ2014 በጀት ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት መረጃ ያመለክታል፡፡