የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ለቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሐምሌ 19/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እንደሌሎች የሀገሪቱ ወጣቶች የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ ለቀረበላቸው ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ “ውድ የኢትዮጵያ መዲና የአዲስ አበባ ወጣቶች እስካሁን ጀግናውን የመከላከያ ሰራዊታቻንን ለመቀላቀል የተመዘገባችሁና ገና ያልተመዘገባችሁ ፍጠኑ ከወንድሞቻችሁና ከእህቶቻችሁ ጋር ተሰለፉ” ሲሉ ጠይቀዋል።

በመላ ሀገሪቱ ወጣቶች በትናንትናው ዕለት በሀገር ላይ የታወጀውን ሴራ ለመመከት ለቀረበላቸው ጥሪ የሰጡት ምላሽ የሚያስመሰግን መሆኑንም አውስተዋል።

“የጀግኖች አባቶቻችን የሀገር ፍቅር፣ የጀግንነት እና የአይበገሬነት ወኔ ዳግም በዚህ ትውልድ ይደምቃል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፥ የህወሓት ጁንታን አርቀን በመቅበር በሀገር ላይ የተከፈተውን የውክልና ጦርነት በድል እናጠናቅቀዋለን” ብለዋል፡፡