የአዲስ አበባ ከፍተኛ አመራሮች ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ የውይይት አደረጉ

ጥቅምት 11/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ የውይይት መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
“ለአዲስ ምዕራፍ ተልዕኮ ዝግጁ ነን” በሚል መሪ ቃል በተጀመረው የውይይት መድረክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በቅርቡ የተሾሙ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ህዝባችን ታገለግሉኛላችሁ ብሎ ድምጹን ብቻ ሳይሆን ተስፋም ጭምር ጥሎብናል ብለዋል።
በለውጥ ሂደት በርካታ ሳንካዎች አሉ፤ እነዚህን ሳንካዎች በጥንቃቄ በማለፍ ህዝብ የጣለብንን ኃላፊነት ለመወጣት ሁሉም አመራር በተደራጀ እና በተቀናጀ መንገድ መስራት እንደሚገባው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
“የ6ኛው ክልላዊ እና ሀገራዊ ምርጫ አፈጻጸም ስኬቶች እና ተግዳሮቶች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር” በሚል በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ምሁራን የተደረገ ዳሰሳዊ ጥናት ላይ ውይይት እየተደረገበት እንደሆነ ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!