የአፍሪካ ህብረት በቻድ የወታደራዊ አመራር እንዲያበቃ ጠየቀ

ሚያዚያ 17/2013 (ዋልታ) – የአፍሪካ ህብረት በቅርቡ በአማፂያን መሪዋ የተገደለባት ቻድ ወታደራዊ አመራር እንዲያበቃ ጥሪ አድርጓል።
የፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ግድያን ተከትሎ ሰራዊቱ ልጃቸው ለ18 ወራት ያህል ወታደራዊውን ጉባኤ ይመራል በማለት አውጀዋል። ይህም ማለት ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ነው።
የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ወታደራዊ አገዛዙ ስልጣን የነጠቀበት መንገድ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮብኛል ብሏል።
በአሁኑ ወቅት ፖርላማው የተበተነ ሲሆን፣ የ37 አመቱ ጄኔራል ማሃማት ዴቢ ኢትኖም በመሪነት ቦታ ተቀምጠዋል።
የምክር ቤቱ 15 አባላት በያዝነው ሃሙስ ተሰብስበው በጉዳዩ ላይ የተወያዩ ሲሆን፣ የኢድሪስ ዴቢ ስርዓተ ቀብር አርብ ከተፈጸመ በኋላ ነው መግለጫ ያወጡት።
መግለጫው በግልፅ እንዳሰፈረው በቻድ ሲቪል አስተዳደር በፍጥነት ሊመለስ እንደሚገባ አሳስቧል።
በአገሪቱ ህገ መንግሥት መሰረት ፕሬዚዳንት በሚሞትበት ጊዜ የፓርላማው አፈ ጉባኤ ስልጣኑን ተረክቦ የመጪው ምርጫ መታቀድ አለበት።
በቅርቡ በሰሜኑ ክፍል ካኔም ሪቤል ፋክት ከተሰኘው አማፂ ቡድን ጋር በነበረ ግጭት ክፉኛ ተጎድተው ህይወታቸው ያለፈው የ68 አመቱ ኢድሪስ ዴቢ፣ ለ6ኛ ጊዜ ተመርጠው አገሪቷን እየመሩ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።