የኢትዮጵያና ቻይና ትብብር በአፍሪካ እና ቻይና መካከል ላለው ግንኙነት ትልቁ ማሳያ መሆኑ ተገለጸ

መጋቢት 18/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያና የቻይና ሁለንተናዊ ትብብር በአፍሪካ እና ቻይና መካከል ላለው ግንኙነት ትልቁ ማሳያ መሆኑ ተገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዙ ቢንግ ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በወቅቶችና ሁኔታዎች የማይቀያየር ስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ ላይ መድረሰን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ግንኙነት አጠናክሮ ለመጓዝ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት እንዳለውም አረጋግጠዋል።

የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዙ ቢንግ የኢትዮጵያና የቻይና ሁለንተናዊ ትብብር በአፍሪካ እና ቻይና መካከል ላለው ግንኙነት ትልቁ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

ቻይና የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ኮንፈረንስ እና የቻይና አፍሪካ ትብብር ፎረም ጉባኤዎች በመጪው ሰኔ እና መስከረም በቤጂንግ እንደሚካሄዱም በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።

ለጉባኤዎቹ ስኬት ኢትዮጵያ ቁልፍ ሚና እንዳላት የጠቀሱት ልዩ መልዕክተኛው ለዚህም የድርሻዋን እንድታበረክት መጠየቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።